የነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
Episode 11 min 40s

የነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና

የነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና በአማራ ክልል ለተፈጠረው ቀውስ ኃላፊነት ወስደው እንዲፈርሙና ከእሥር እንዲፈቱ ጥያቄ እንደቀረበላቸው የገለፁ 30 የሽብር ተከሳሾች አንፈርምም ማለታቸው ተነገረ። በአማራ ክልል በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ከፃግምና አበርገሌ ወረዳዎች ተፈናቅለው ሰቆጣ ከተማ የተጠጉ ወገኖች ለከፋ የምግብ እና የመጠለያ እጥረት ተዳርገናል እያሉ ነው። የአስተዳደር ዞኑ አደጋ ስጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽን በበኩሉ አዲስ ለመጡት ካልሆነ ድጋፍ እየተደረገ ነው ይላል። ደቡብ አፍሪቃ ዜጎቻቸውን ወደ የሃገራቸው የመለሰችላቸው የሌሎች የአፍሪቃ ሃገራት መንግሥታት ወጪውን እንዲከፍሏት መጠየቋ ተሰማ።

Community discussion