የሐምሌ 22 ቀን 2018 የዓለም ዜና
Episode 11 min 22s

የሐምሌ 22 ቀን 2018 የዓለም ዜና

-ሳዑዲ አረቢያ «ሐሺሽ ይዘዉ ተገኝተዋል» በሚል የወነጀለቻቸዉን አምስት ኢትዮጵያዉያን ሥደተኞችን በሞት ቀጣች።ሑዩማን ራይትስ ዋች እንዳስታወቀዉ ሳዑዲ አረቢያ የግሪጎሪያኑ 2026 ከባተ ካለፈዉ ጥር ወዲሕ በተመሳሳይ ወንጀል ተሳትፈዋል ያለቻቸዉን 17 ኢትዮጵያዉያንን ያለ ተገቢ የፍርድ ሒደት በሞት ቀጥታለች።----የተለያዩ የወንጀል መረቦች «ሥራ ታገኛላችሁ» በሚል ከየሐገሩ እያስኮበለሉ በየማጭበርበሪያ ማዕከላቱ የሚሰቃዩና የሚያሰሯቸዉ ሰዎች ብዛት በመቶ ሺሕ ሊቆጠር እንደሚችል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።---ዩናይትድ ስቴትስ ከኢራን ጋር በገጠመችዉ ጦርነት ሳዑዲ አረቢያም ቀስ በቀስ እየተዘፈቀችበት ነዉ።

Community discussion