ማሕደረ ዜና፣ የሸረሪና ዉጊያ፣ «የክተት» አዋጅና የፕሪቶሪያ ዉል
Episode 13 min 26s

ማሕደረ ዜና፣ የሸረሪና ዉጊያ፣ «የክተት» አዋጅና የፕሪቶሪያ ዉል

ከሰኔ 30 በኋላ ከህወሐት ያፈነገጠዉ አንጃ አዲስ አበባ ዉስጥ የትግራይ ተወላጆችና ደጋፊዎቻቸዉን «ጦርነት አንፈልግም» በሚል በአደባባይ ሲያሰልፍ፣ መቀሌ ዉስጥ ደግሞ ህወሓት የጠራዉ ተቃራኒ ህዝባዊ ሥብሰባ ተደርጓል።ስልፍና ስብሰባዉ የቃላት ጦርነቱን ወደየደጋፊዎቻቸዉ ለማስረፅ ያለመ መሆኑ አላከራከረም። የህወሐት ዋና ፀሐፊ ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር ለትግራይ ወጣቶች «አሁን ብቻችን አይደለንም» ማለታቸዉ ግን ከቃል አቀባያቸዉ አባባል ጋር የሚጣረስ በተገላቢጦሹ የጠቅላይ ሚንስትር አብይን ወቀሳ የሚያረጋግጥ ነዉ

Community discussion