ሱዳን “የጭካኔ ቤተ-ሙከራ” የሆነችበት ጦርነት አራተኛ ዓመቱን ጀመረ
Episode 11 min 49s

ሱዳን “የጭካኔ ቤተ-ሙከራ” የሆነችበት ጦርነት አራተኛ ዓመቱን ጀመረ

በሱዳን ጦርነት በሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በድሮኖች ጥቃት ጭምር ተገድለዋል። ጦርነቱ አራተኛ ዓመቱን ሲጀምር 34 ሚሊዮን ሰዎች ሰብአዊ ርዳታ ይጠብቃሉ። ሀገሪቱን ለሁለት የከፈላትን ጦርነት ለማቆም የሚደረገው ጥረት እስካሁን አልተሳካም። ጦርነቱ ከሱዳን ድንበር በመሻገር ወደ ጎረቤት ሀገሮች ተዛምቶ “ከቁጥጥር ውጪ” ሊሆን እንደሚችል ሥጋት አለ። የሱዳን ብሔራዊ ጦር አዛዥ ሉቴናንት ጄኔራል አብዱል ፋታኅ አል-ቡርኻን እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች አዛዥ መሐመድ ሐምዳን ደጋሎ ጦርነቱን ለማቆም እስካሁን ተጨባጭ ፈቃደኝነት አላሳዩም።

Community discussion